Jr G Lud Offline

33 In a relationship Male    24
         

ጋዜጠኛውና አዛውንቱ

አንድ ወጣት ጋዜጠኛ የአዛውንቶች መጦርያ ቤት ውስጥ የ 96 አመቱን ግን እጅግ በጣም ዝነኛ አዳኝ የነበሩትን ሰውዬ ቃለ መጠይቅ እያደረገላቸው ነው ::

ጋዜጠኛ :- "በአደን ላይ እያሉ በጣም አስፈሪ ወይም አስገራሚ የሚሉት አጋጣሚ ከነበረዎት ቢያጫውቱኝ "

አዛውንቱ አዳኝ :- "ይኸውልህ አንድ ወቅት ላይ ህንድ አገር ውስጥ ነው , ጥቅጥቅ ያለ ደን ውስጥ የሀገሩ ተወላጅ ከሆነ ታማኝ ረዳቴ ጋር ለአደን ወጣን :: ቀጭን መንገድ ይዘን ፊትና ሁዋላ ሆነን እየተጉዋዝን እያለ በድንገት እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ ነብር ከፊት ለፊታችን ድቅን አለብን :: እንዴት እንደደነገጥኩ አጠይቀኝ , መሳርያዬን ከረዳቴ ልወስድ ዞር ስል እሱ ፈርጥጦ ጠፍቶዋል :: ከዛማ ነብሩ ወደኔ ተወርውሮ በሚያስበረግገው ድምጹ ሮአርርርርርርርርርርርርርርር ሲል ................. አሬ አመለጠኝ ::

ጋዜጠኛ :- "በርግጥ እንዲህ ያለ አስደንጋጭ አጋጣሚ ሲያጋጥም ሁሉም ሰው ሊያደርገው የሚችለው ነገር ነው ..."

አዛውንቱ አዳኝ :- "አረ !! የዛን ግዜ እኮ አይደለም :: አሁን ነው እንጂ ሮአርርርርርርርርርር ብዬ ስጮህ ::